የግላዊነት ፖሊሲ

SEIU የግላዊነትዎ አስፈላጊነት ላይ በጥብቅ ያምናል። ይህ የግላዊነት ፖሊሲ SEIU በ SEIU ድረገፅ (“ድረገፅ”) በኩል የምንሰበስበው የግል መረጃ እንዴት እንደሚይዝና በመረጃው ምን እንደምናደርግ ይገልፃል። ድረገፁን በመጠቀም ወይም በመድረስ በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ የተገለፁትን ልማዶችን እየተቀበሉ ነው። ይህ የግላዊነት መግለጫ የሚተገበረው በኦንላይን በድረገፁ በኩል በተሰበሰበ መረጃ ላይ ብቻ ሲሆን ከኦንላይን ወይም ከድረገፃችን ውጭ ወይም ሌላ አካል ውጭ የተገኘን መረጃ የምንሰበስብባቸውን ወይም የምንጠቀምባቸውን መንገዶች አይገልፅም። ይህንን የግላዊነት ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ልናሻሽለው እንችላለን።

መረጃን እንዴት፣ መቼ እና ለምን እንደምንሰበስብ

 • ድረገፃችንን ሲያስሱ ስለእርስዎ ምን እንደምንሰብስብ። ምንም አይነት የግል መረጃን ሳይመዘግቡ ወይም ሳያቀርቡ በድረገፁ ላይ ይዘት ማየት ይችላሉ። በኮምፒውተር፣ መተግበሪያ ሞባይል ስልክ ወይም ሌላ የበይነ-መረብ ፖርታል በኩል ወደ ድረገፁ ሲገቡ በድረገፁ ላይ ያለዎትን ተሞክሮ ለማሻሻል፣ የሚመለከታቸውን ህጎች ማክበር እና አጠቃላይ የድረገፅ አጠቃቀምን ለመከታተል እንደ አሳሽዎ እና የክንውን ስርዓት አይነት እና የአይፒ አድራሻ ያሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ የተለያዩ የመከታተያ መሳሪያዎችን እንጠቀማለን። በድረገፁ በኩል የተላከልን መረጃ የሚከተሉትን ያጠቃልላል ቢሆንም በዚህ ብቻ አይወሰንም፡ ስለሚደርሷቸው ገፆች ውሂብ፣ የኮምፒውተር አይፒ አድራሻ፣ የመሳሪያ መታወቂያ ወይም ልዩ መለያ፣ የመሳሪያ አይነት፣ የጂኦ-አካባቢ መረጃ፣ የኮምፒውተር እና ግንኙነት መረጃ፣ የሞባይል የአውታረ መረብ መረጃ ፣ በገፅ እይታዎች ላይ ያሉ ትንታኔዎች፣ ወደ ጣቢያዎች እና ከጣቢያዎች ትራፊክ፣ ሪፈራል ዩአርኤል፣ የማስታወቂያ ውሂብ እና መደበኛ የድር ሎግ ውሂብ እና ሌሎች መረጃዎች። በስም-አልባ መረጃዎችን በኩኪዎች እና ድር ቢኮኖች አጠቃቀማችን እና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችም በኩል እንሰበስባለን።
 • ለማነጋገር በእኛ መነሳሳት። እርስዎን ለማግኘት ስንል ያቀረቡትን ማንኛውንም መረጃ ልንጠቀም እንችላለን።
 • ምዝገባ የሚያስፈልገው ተግባር። እንደ ተባባሪ አባል SEIUን መቀላቀል ያሉ በድረገጹ ላይ ያሉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች እዚህ በተገለፁት ውሎች መሰረት እንዲመዘገቡ ይጠይቃሉ። የተመዘገበ ተጠቃሚ ለመሆን ስምዎን፣ የኢሜይል አድራሻዎን፣ የፖስታ ኮድዎን፣ ስራዎን እና አሰሪዎን እንዲገልፁ እንጠይቅዎታለን። ለመመዝገብ ከወሰኑ፣ ወደ ድረገፁ ሲመለሱ በቀላሉ መግባት እንዲችሉ ለማገዝ የተወሰኑ መረጃዎችን የሚያከማች የማያቋርጥ ኩኪን እንጠቀማለን። ሆኖም ግን፣ የትኛውም የግል መረጃዎ በዚያ ኩኪ ውስጥ አልተቀመጠም። በተጨማሪም SEIU በዚህ ድረገፅ በኩል የቀረበ ማንኛውንም የክፍያ ወይም ፋይናንስ መረጃ የማግኘት መብት የለውም።
 • የአጠቃቀም መረጃ። እንደ ጣቢያውን ሲጠቀሙ፣ ጠቅ ስላደረጉበት እና/ወይም ስለተሳተፉበት የጣቢያው አካባቢዎች፣ ስለፈለጉት መለያዎች እና ለአርኤስኤስ ፊድ ደንበኝነት መመዝገብ ወይም አለመመዝገብዎን የመሳሰሉ ስለ ድረገፁ አጠቃቀምዎ መረጃ እንመዘግባለን። ይህንን መረጃ ለመከታተል የማያቋርጥ ኩኪ መጠቀም የሚቻል ቢሆንም የገባውን የፋይናንስ መረጃ አይከታተልም። የትኛዎቹ ኢሜይሎች እንደተከፈቱ እና/ወይም ጠቅ እንደተደረጉ ለመከታተል በኤችቲኤምኤል ላይ የተመሰረቱ ኢሜይሎች ውስጥ የፒክሰል መለያዎችን እና/ወይም መከታተል የሚችሉ ማስፈንጠሪያዎችን ልንጠቀም እንችላለን። በተጨማሪም፣ በሶስተኛ ወገኖች እንደ ማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆች (ለምሳሌ፡- ፌስቡክ እና ትዊተር) የተከማቸ ግላዊ መረጃ እንድናገኝ ከመረጥን፣ የምንቀበለው መረጃ እንደ ድረገፅ እንደሚለያይ እና በዚያ ጣቢያ ቁጥጥር ስር መሆኑን ማወቅ አለብዎት። በሶስተኛ ወገን የሚተዳደረውን መለያ ከድረገፁ አጠቃቀም ጋር በማያያዝ SEIU ይህን መረጃ እንዲደርስ ፈቃድ እየሰጡ ነው፣ እናም SEIU ይህንን መረጃ በዚህ የግላዊነት መመሪያ መሰረት ሊሰበስብ፣ ሊያከማች እና ሊጠቀምበት እንደሚችል ተስማምተዋል።
 • ድምፅ መስጫዎች እና የዳሰሳ ጥናቶች። ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ደምፅ መስጫዎችን እና የዳሰሳ ጥናቶችን ልናከናውን እንችላለን። በግል ምላሾችዎን ለተወሰነ ዓላማ ለመጠቀም ፈቃድ ካልጠየቅን በስተቀር በድምፅ መስጫዎቻችን፣ የዳሰሳ ጥናቶች እና መጠይቆች የተሰበሰበ መረጃ በአጠቃላይ ጥቅም ላይ ይውላል።
 • ሆን ብለን ከ 13 አመት በታች ከሆኑ ህፃናት ምንም አይነት መረጃ አንሰበስብም።

የግል መረጃ አጠቃቀም

 • SEIU በድረገፁ ላይ የሚሰበስበው ግላዊ መረጃ እኛን፣ የግዛታችን እና የአካባቢ አጋር ድርጅቶችን እና ከ SEIU ጋር የተገናኙ ድርጅቶች አባሎቻችንን በብቃት እና በውጤታማነት እንድንወክል፣ የጥብቅና አጀንዳችንን እንድንከታተል እና ጠቃሚ የአባላት ጥቅማጥቅሞችን መስጠት እንድንችል ይረዳናል።
 • እነዚህን ግቦች እና ተግባራት ለማስቀጠል፣ ስለእርስዎ የምንሰበስበውን የግል መረጃ ከግዛታችን እና ከአካባቢው አጋር ድርጅቶች እና ከሌሎች ከSEIU ጋር ለተያያዙ ድርጅቶች እንዲሁም በእኛ ምትክ አገልግሎት ለሚሰጡ ሶስተኛ ወገኖች ልናጋራ እንችላለን። በተጨማሪም፣ ስለእርስዎ የምንሰበስበውን ማንኛውንም የግል መረጃ በሚመለከተው ህግ መሰረት ፍላጎታችንን ለሚጋሩ ሶስተኛ ወገኖች ልናጋራ እንችላለን። ወደዚህ ድረገፅ ያስገቡትን ማንኛውንም የፋይናንስ መረጃ በህጋዊ መንገድ ካልጠየቁ በስተቀር አናጋራም።
 • እንደዚህ አይነት መልዕክቶችን ከመቀበል መርጠው ካልወጡ በስተቀር፣ ስለ SEIU እንቅስቃሴዎችና አቅርቦቶች አስመልክቶ ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት የኢሜይል አድራሻዎን እንጠቀማለን። እንዲሁም የኢሜይል አድራሻዎን እንደ ዋና ዋና የድረገፅ ለውጦችን ለእርስዎ ማሳወቅ፣ በጣቢያው ላይ ከወሰዷቸው እርምጃዎች ወይም ለደንበኞች አገልግሎት ዓላማዎች መልዕክቶችን መላክ መሰል ለአስተዳደራዊ ዓላማዎች እንጠቀማለን። ምንም እንኳን እነዚህ ግንኙነቶች መረጃ ሰጪና ጠቃሚ ሆነው እንደሚያገኙ ተስፋ ብናደርግም፣ ሆኖ ካላገኙት ሁልጊዜ በእያንዳንዱ ኢሜይል ውስጥ የተካተቱትን ቀላል መመሪያዎችን በመከተል ከደንበኝነት ምዝገባ መውጣት ይችላሉ።
 • ኢሜይል ወይም ሌሎች ግንኙነቶችን ወደ እኛ ሲልኩ፣ ጥያቄዎችዎን ለማስተናገድ፣ ለጥያቄዎችዎ ምላሽ ለመስጠት እና አገልግሎቶቻችንን ለማሻሻል እነዚያን ግንኙነቶች ልናቆየው እንችላለን።
 • የተጠቃሚ ተሞክርዎ ጥራት እና የድረገፁን ዲዛይን ለማሻሻል እና የተጠቃሚ ባህሪን፣ ምርጫዎችን፣ አዝማሚያዎችን እና ድርጊቶችን በማከማቸት፣ በመከታተል እና በመተንተን አዲስ ባህሪያትን፣ ተግባራትን እና አገልግሎቶችን ለመፍጠር ሁለቱንም በግል የሚለይ መረጃዎን እና አንዳንድ ግላዊ ያልሆኑ መለያ መረጃዎችን (እንደ ስም-አልባ የአጠቃቀም ውሂብ፣ አይፒ አድራሻዎች፣ የአሳሽ አይነት፣ የጠቅታ ዥረት ውሂብ፣ ወዘተ.) እንጠቀማለን።

ሌሎች መግለጫዎች

እንደ መጥሪያ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዞች ባሉ ህጋዊ ጥያቄዎች መሰረት ወይም የሚመለከታቸው ህጎችን በማክበር የተጠቃሚ መረጃን መግለፅ ልንጠየቅ እንችላለን። ስለእርስዎ መረጃ የሚጠይቅ የጥሪ ወረቀት ከደረሰን እና የኢሜይል አድራሻዎን ለእኛ ከሰጡ፣ መጥሪያውን እርስዎ ባቀረቡት ኢሜይል አድራሻ ልናሳውቅዎ እንሞክራለን። በተጨማሪም፣ ህጉን ለማክበር፣ ጥቅሞቻችንን ወይም ንብረታችንን ለመጠበቅ፣ በድረገፁ በኩል የሚፈፀሙ ማጭበርበርን ወይም ሌሎች ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ወይም የ SEIU ስምን በመጠቀም የአካል ጉዳትን ለመከላከል አስፈላጊ መሆኑን ስናምን የተጠቃሚ ስምምነታችንን ለማስፈጸም ወይም ወደ ጣቢያችን፣ አባሎቻችን፣ ህዝባዊ ወይም SEIU የጎብኝዎችን መብቶች፣ ንብረት ወይም ደህንነት ለመጠበቅ መለያ ወይም ሌላ መረጃ ልናጋራ እንችላለን። SEIU (ወይም በአጠቃላይ ሁሉም ንብረቶቹ) ከሌላ አካል ጋር ሲዋሃዱ የማይመስል ክስተት ከሆነ፣ የጎብኚዎቻችን መረጃ ከተተላለፉ ንብረቶች መካከል አንዱ ይሆናል። በተጨማሪም SEIU በሞባይል መተግበሪያዎችን ወይም በሞባይል የተመጣጠነ ድረገፅ በሞባይል መሳሪያ በመጠቀም ተጠቃሚዎች ከድረገፁ ጋር የመገናኘት ችሎታን ሊሰጥ ይችላል። የዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ድንጋጌዎች በሁሉም የሞባይል መዳረሻና የሞባይል መሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ። የሞባይል መተግበሪያዎቻችንን ሲያወርዱ ወይም ሲጠቀሙ ወይም ከሞባይል ጋር ከሚስማሙ ድረገፆቻችን ውስጥ አንዱን ሲደርሱ፣ ስለ አካባቢዎ እና ስለ ሞባይል ስልክዎ፣ ለመሳሪያዎ ልዩ መለያን ጨምሮ መረጃ ልንቀበል እንችላለን። ይህን መረጃ እንደ ማስታወቂያ፣ የፍለጋ ውጤቶችና ሌሎች ግላዊነት የተላበሱ ይዘቶችን የመሳሰሉ አካባቢ ተኮር አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ ልንጠቀምበት እንችላለን። አብዛኛዎቹ የሞባይል ስልኮች በመሳሪያው የቅንጅቶች ምናሌ ውስጥ የአካባቢ አገልግሎቶችን መቆጣጠር ወይም ማገድ ያስችሎታል። የመሳሪያዎን የአካባቢ አገልግሎቶችን እንዴት እንደሚያግዱ ጥያቄዎች ካሎት፣ የሞባይል አገልግሎት አቅራቢዎን ወይም የመሳሪያዎን አምራችዎን እንዲያነጋግሩ እንመክርዎታለን።

የመረጃ ደህንነት እና የውሂብ ታማኝነት

SEIU ያልተፈቀደ የመድረስ ወይም ያልተፈቀደ ለውጥ፣ ይፋ ማድረግ ወይም የውሂብ መጥፋትን ለመከላከል የደህንነት እርምጃዎችን ይወስዳል። እነዚህም እርምጃዎች የእኛን የውሂብ አሰባሰብ፣ የማከማቸት እና የማቀናበር ልምምዶች እና የደህንነት እርምጃዎች ውስጣዊ ግምገማዎችን እንዲሁም የግል መረጃን የምናከማችበት ያልተፈቀደ የስርዓት መዳረሻን ለመከላከል የአካላዊ ደህንነት እርምጃዎችን ያካትታሉ።

ተጨማሪ መረጃ

የእኛ ድረገጽ የ SEIU ያልሆኑ ጣቢያዎችን እንዲደርሱ ሊፈቅድልዎ ይችላል። ከድረገጻችን ወደ SEIU ያልሆነ ጣቢያ ከተገናኙ የወገኑ የግላዊነት ፖሊሲ እና የተጠቃሚ ስምምነቱ በእርስዎ ላይ እንደሚተገበር ማስታወሱ አስፈላጊ ነው። የግል መረጃን ለሶስተኛ ወገን ከመስጠትዎ በፊት ስለ እያንዳንዱ የግላዊነት ፖሊሲያቸው እንዲያውቁ እናበረታታዎታለን።

SEIU ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ነው። በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ላይ ማናቸውንም ለውጦች በዚህ ገፅ ላይ የምንለጥፍ በመሆኑ ይህን ገፅ በመደበኛነት እንዲመለከቱት እናበረታታዎታለን። በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ማንኛቸውም ለውጦችን ተከትሎ ይህን ድረገጽ መጠቀምዎ እንደዚህ አይነት ለውጦችን መቀበልዎ ይሆናል።

ስለዚህ የግላዊነት ፖሊሲ፣ ድረገፁ ወይም መለያዎ ማናቸውም አይነት ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ እኛን ለማግኘት ነፃነት ይሰማዎት

ተፈፃሚ የሚሆንበት ቀን፡- ኦገስት 2፣ 2018

የአገልግሎት ውሎች

የተጠቃሚ ስምምነት

ወደ SEIU ድረገፅ እንኳን በደህና መጡ። እባክዎ ጣቢያውን መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት የተጠቃሚ ስምምነታችንን በጥንቃቄ ያንብቡ። እናመሰግናለን።

 1. የእርስዎ እንኳን ወደ SEIU.org በደህና መጡ ተቀባይነት። ይህንን ድረገፅ በመጠቀም እና/ወይም በመጎብኘት፣ (1) በእነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች (“የተጠቃሚ ስምምነት”) እና (2) የ SEIU ግላዊነት ፖሊሲ፣ እዚህ በማጣቀሻነት የተካተቱትን መቀበልዎን ጠቁመዋል። በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት እና የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ በተካተቱት ሁሉም ውሎች እና ሁኔታዎች ካልተስማሙ፣ ድረገፁን ለመጠቀም አልተፈቀደልዎትም። ምንም እንኳን በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ላይ ዋነኛ ለውጦች ሲደረጉ እርስዎን ለማሳወቅ የምንሞክር ቢሆንም በጣም ወቅታዊውን ስሪት በየጊዜው መፈተሽ አለብዎት። SEIU ብቻውን ይህንን የተጠቃሚ ስምምነት በማንኛውም ጊዜ ሊያሻሽለው ይችላል። እንደዚህ አይነት ለውጦችን መለጠፍን አስከትሎ ይህን ድረገፅ መጠቀማችንን በመቀጠል፣ በተሻሻለው መሰረት በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ለመገዛት ተስማምተዋል። በጣቢያዎቻችን በኩል SEIU ለተጠቃሚዎች የተበጁ ይዘቶችን ጨምሮ የበለፀገ የትምህርት ግብዓቶች እንዲያገኙ ያቀርባል። ገፆቻችን ጠቃሚ ሆነው እንዳገኗቸው ተስፋ እናደርጋለን። ድረገፁን ወይም ተዛማጅ ድረገጾቹን ወይም የትኛውንም ይዘታቸውን በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ምክንያት የማሻሻል፣ የማገድ ወይም የማቋረጥ መብታችን የተጠበቀ ነው። ለማንኛውም ማሻሻያ፣ መታገድ ወይም መቋረጥ ተጠያቂ የማንሆን መሆናችንን ተስማምተዋል። የምዝገባ መረጃዎ፣ እንዲሁም ደግሞ በገፃችን ላይ ስለራስዎ የሚሰጡን ሌላ በግል የሚለይ መረጃ ለግላዊነት መመሪያችን ተገዢ ነው።
 2. የድረገፁ አጠቃላይ አጠቃቀም – ፈቃዶች እና ገደቦች SEIU በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ውስጥ በተገለፀው መሰረት ድረገፁን ለመጠቀም እና ለመድረስ ፈቃድ ይሰጥዎታል፡-
  1. የተጠቃሚ ስሞችን ወይም የኢሜይል አድራሻዎችን ጨምሮ የሌሎችን በግል የሚለይ መረጃ እርስዎ ከድረገፁ አይሰበሰቡም።
  2. ያለ SEIU የፅሁፍ ፈቃድ ድረገፁን ለማንኛውም የንግድ አላማ አይጠቀሙበትም። ማንኛውንም ያልተፈለገ ማስታወቂያ፣ የማስተዋወቂያ መረጃ፣ የጅምላ ኢ-ሜይል ወይም ሌላ መጠየቅ ላለማስተላለፍ ወይም እንዲገኝ ላለማድረግ ተስማምተዋል። በድረገፁ ላይ የሚለጥፉትን ነገሮች አስመልክቶ ማንኛውንም የድረገፁ ተጠቃሚዎች ለንግድ አላማ ላለመጠየቅ ተስማምተዋል።
  3. የሰው ልጅ በተለመደው የኦንላይን ድር አሳሽ በመጠቀም በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከሚጠይቀው ክፍለ ጊዜ በላይ የ SEIU ሰርቨሮችን መልዕክት የሚጠይቅን ድረገፅ የሚጠቀሙ ገደብ-የለሽ “ሮቦቶች፣” “ስፓይደርስ፣” ወይም “ከኦንላይ ውጭ አንባቢዎች” ን ጨምሮ ምንም አይነት አውቶማቲክ ሲስተም አይጠቀሙም ወይም አይከፍቱም። ከላይ የተጠቀሰው ቢሆንም፣ SEIU ለህዝብ የፍለጋ ኢንጅን ኦፕሬተሮች ስፓይደሮችን ከጣቢያው ላይ ለንጥሎች ብቸኛ ዓላማ እና በይፋ የሚገኙ የማቴሪያሎች ኢንዴክሶችን፣ ይህም የማቴሪያሎች ካቼዎች ወይም ማህደሮች አይነት ያልሆኑትን ለመፍጠር አስፈላጊ በሆነው መጠን ስፓይደሮችን እንዲጠቀሙ ፈቃድ ሰጥቷል። SEIU እነዚህን ልዩ ሁኔታዎች በጠቅላላ ሆነ በተወሰኑ ጉዳዮች የመሻር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  4. የኮምፒውተር ሃርድዌር ወይም የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን ተግባር ለማስተጓጎል፣ ለማጥፋት ወይም ለመገደብ የተነደፈ ማንኛውንም “ቫይረስ፣” “ዎርም፣” “ትሮጃን ፈረስ” ወይም ማንኛውንም የኮምፒተር ኮድ፣ ፋይል ወይም ፕሮግራም አያስተላልፉም ወይም እንዲገኙ አያደርጉም።
  5. የድረገፁን የትኛውንም ክፍል አይቀይሩም ወይም አያስተካክሉም።
  6. ከደህንነት ጋር የተያያዙ የድረገፁን ወይም የኛን ድረገፆች ወይም ሰርቨራችን (ወይም ከድረገፃችን ጋር የተገናኙ አውታረ መረቦችን) አያቋርጡም፣ አያግዱም ወይም ጣልቃ አይገቡም።
  7. በድረገፁ ወይም በመገናኛ ስርዓቶቹ ላይ አንድን ሰው ወይም የሚመለከተውን አካል አያስቸግሩም፣ አያስፈራሩም፣ አያሳፍሩም ወይም ጭንቀትን፣ ያልተፈለገ ትኩረትን ወይም ምቾት መንሳት አያመጡም።
  8. በ SEIU ብቻ እንደተወሰነው ህገ-ወጥ፣ ጎጂ፣ አስጊ፣ አንቋሻሽ፣ ትንኮሳ፣ ስም አጥፊ፣ አስፈራሪ፣ ጸያፍ፣ የጥላቻ፣ ወይም ዘር፣ ጎሳ ወይም በሌላ መልኩ የሚቃወሙ ይዘቶችን በድረገፅ ላይ ወይም በሌላ መንገድ አያስተላልፉም።
  9. SEIU በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ምክንያት እና ለእርስዎ ያለማሳወቂያ የድረገፁን ማንኛውንም ገፅታ የመቀየር ወይም ማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. SEIU ያለቅድመ ማስታወቂያ እና በ SEIUብቸኛ ምርጫ የተጠቃሚውን የድረገፁን መዳረሻ የማገድ ወይም ማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ይህ የፈቃዶች እና ገደቦች ዝርዝር፣ ከታች ከተብራሩት ሌሎች ውሎች ጋር ለመጠናቀቅ የታሰበ ሳይሆን ገላጭ ብቻ ነው። ምግባሩ ለድረገፁ የምግባር መስፈርቶችን የሚጥስ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን በእኛ ብቸኛ እና የመጨረሻ ውሳኔ ውስጥ መብታችን የተጠበቀ ነው።
 3. በጣቢያው ላይ ያለዎት የይዘት አጠቃቀም የሚከተሉት ክልከላዎች እና ሁኔታዎች በተለይ በድረገፁ ላይ ባለው የይዘት አጠቃቀምዎ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ።
  1. በድረገፁ ላይ ያለው ይዘት (ከእርስዎ የተጠቃሚ ይዘት ሌላ) ያለ ገደብ ፅሁፎችን፣ ሶፍትዌሮችን፣ ስክሪፕቶችን፣ ግራፊክስን፣ ፎቶዎችን፣ ድምጾችን፣ ሙዚቃን፣ ቪዲዮዎችን፣ በይነተገናኝ ባህሪያትን እና የመሳሰሉትን ጨምሮ (በጋራ “SEIU ይዘት”) በ SEIU ባለቤትነት የተያዘ ወይም ፍቃድ የተሰጠው ነው። በተመሳሳይ መልኩ፣ በድረገፁ ላይ የተካተቱት የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች እና አርማዎች በ SEIU (“SEIU ምልክቶች”) ባለቤትነት ወይም ፈቃድ የተሰጣቸው ናቸው። በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ወይም በድረገፁ ላይ ሌላ ቦታ (ለምሳሌ፡- በዘመቻ መግለጫ) ከተደነገገው በስተቀር ያለ የ SEIU ቅድመ የፅሁፍ ፍቃድ የ SEIU ይዘት እና የ SEIU ምልክቶች ሊወርዱ፣ ሊገለበጡ፣ ሊባዙ፣ ሊሰራጩ፣ ሊተላለፉ፣ ሊሰራጩ፣ ሊታዩ፣ ሊሸጡ ወይም ለማንኛውም አላማ ፍቃድ ያለው ወይም በሌላ መንገድ ጥቅም ሊውሉ አይችሉም። SEIU በ SEIU ይዘት እና በ SEIU ምልክቶች ላይ በግልፅ ያልተሰጡ ሁሉንም መብቶች ይጠብቃል።
  2. ድረገፁ ለግል ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ብቻ የተዘጋጀ ነው። እንደ የዚህ አጠቃቀም አካል፣ ከጣቢያው ገጾችን ማሳየት፣ ማውረድ እና/ወይም ማተም ይችላሉ፤ ወደ ድረገፁ ማገናኘት ይችላሉ፤ እና የድረገፅ ማቴሪያሎችን ለሌሎች ለግል፣ ለንግድ ላልሆኑ አገልግሎቶች ከድረገፁ ዓላማዎች ጋር በተመጣጣኝ ሁኔታ ማስተላለፍ ይችላሉ።
  3. ድረገፁን ሲጠቀሙ ከተለያዩ ምንጮች ለ SEIU ይዘት፣ የተጠቃሚ ይዘትና ሌሎች የሶስተኛ ወገን ይዘቶች እንደሚጋለጡ እና SEIU ስለ አገልግሎቱ ትክክለኛነት፣ ጠቀሜታ፣ ደህንነት ወይም አእምሯዊ ንብረት መብቶች ወይም ከእንዲህ ዓይነቱ SEIU ይዘት፣ የተጠቃሚ ይዘት ወይም ሌላ የሶስተኛ ወገን ይዘት ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ዋስትና እንደማይሰጥ ተገንዝበዋል። በተጨማሪም ከዚ ጋር በተያያዘ እርስዎ በ SEIU ላይ ያሎትን ወይም ሊኖርዎት የሚችለውን ማንኛውንም ህጋዊ ወይም ፍትሃዊ መብቶች ወይም መፍትሄዎች ለተሳሳተ፣ አፀያፊ፣ ጨዋነት የጎደለው ወይም ተቃውሞ ለሆነ የተጠቃሚ ይዘት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተረድተው እውቅና ሰጥተዋል።
  4. ድረገፅ በ SEIU ያልተያዙ ወይም ያልተቆጣጠሩት የሶስተኛ ወገን ድረገፆች ማስፈንጠሪያዎችን ሊይዝ ይችላል። SEIU በማንኛውም የሶስተኛ ወገን ድረገፆች ይዘት፣ የግላዊነት ፖሊሲዎች ወይም ልምዶች ላይ ምንም አይነት ቁጥጥር የለውም፣ እና ምንም ሃላፊነት አይወስድም። ከድረገፁ ሲወጡ እንዲያውቁ እና እርስዎ የሚጎበኟቸውን ድረገፆች ውሎች እና ሁኔታዎች እና የግላዊነት ፖሊሲ እንዲያነቡ እናበረታታዎታለን።
 4. የዲጂታል ሚሌኒየም የቅጂ መብት ህግ እርስዎ የቅጂ መብት ባለቤት ከሆኑ ወይም ወኪሉ ከሆኑ እና ማንኛውም የ SEIU ይዘት ወይም የተጠቃሚ ይዘት የቅጂ መብትዎን የሚጥስ እንደሆነ ካመኑ፣ በዲጂታል ሚሌኒየም የቅጂ መብት ህግ (“DMCA”) መሰረት የ SEIU የቅጂ መብት ወኪል ከሚከተለው መረጃ ጋር በፅሁፍ (ለበለጠ ዝርዝር 17 USC 512(c)(3) ይመልከቱ) በማቅረብ ማሳወቂያ ማስገባት ይችላሉ።
  • የቅጂ መብት ያለበትን ስራ መለየት ተጥሷል
  • መጣስ ወይም የጥሰት ተግባር ጉዳይ ነው የተባለውን ማቴሪያል መለየት እና መወገድ ያለበት ወይም ሊታገድበት የሚገባውን መረጃ ለማግኘት እና SEIU ንብረቱን እንዲያገኝ የሚያስችል በቂ መረጃ፤
  • በቅጂ መብት ባለቤት፣ በተወካዩ ወይም በህግ ያልተፈቀደ መሆኑን ማቴሪያሉን በቅሬታ መንገድ መጠቀሙን ጥሩ እምነት እንዳለዎት የሚያሳይ መግለጫ፤
  • በማስታወቂያው ውስጥ ያለው መረጃ ትክክል እንደሆነና በሃሰት ምስክርነት ቅጣት ስር እርስዎ እንደተጣሱ የተጠረጠረ ብቸኛ መብት ባለቤት እርስዎ እንደሆኑ ወይም ለመወከል ስልጣን እንዳለዎት የሚገልፅ መግለጫ፤
  • የእርስዎ ስም፣ የፖስታ አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ፤ እና
  • ተጥሷል የተባለው የብቸኛው መብት ባለቤት ወይም ባለቤቱን ወክሎ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ግለሰብ አካላዊ ወይም ኤሌክትሮኒክ ፊርማ። የ SEIU የተመደበው የቅጂ መብት ወኪል የይገባኛል ጥሰት ማሳወቂያዎችን ለመቀበል በ copyright@seiu.org ማግኘት ይቻላል። ከላይ ያሉትን ሁሉንም መስፈርቶች ካላሟሉ የ DMCA ማሳሰቢያዎ ትክክል ላይሆን እንደሚችል አምነዋል። ግልጽ ለማድረግ የ DMCA ማስታወቂያዎች ብቻ ወደ የቅጂ መብት ወኪል መላክ ይኖርባቸዋል። እባክዎ የያነጋግሩን ቅፅን ለሌላ ማንኛውም ግብረመልስ፣ አስተያየቶች፣ የቴክኒክ ድጋፍ ጥያቄዎች ወይም ሌሎች ከ SEIU ጋር ለሚደረጉ ግንኙነቶች ይጠቀሙ።
 5. የዋስትና ማስተባበያ ይህ ድረገፅ “እንደነበረ” ቀርቦልዎታል። የ SEIU ድረገፅ አጠቃቀምዎ በእርስዎ ብቸኛ ሃላፊነት ላይ እንደሚሆን ተስማምተዋል። ህግ በሚፈቅደው ሙሉ መጠን፣ SEIU፣ እንዲሁም ባለስልጣናቱ፣ ዳይሬክተሮቹ፣ ሰራተኞቹ እና ወኪሎቹ (በአጠቃላይ “የSEIU ወገኖች”) ከድረገፁ እና ከአጠቃቀምዎ ጋር በተገናኘ ሁሉንም ዋስትናዎች ከድረገፁ እና ከአጠቃቀምዎ ጋር በተገናኘ በግልጽ ወይም በተዘዋዋሪ አይቀበሉም። የ SEIU ወገኖች ለጣቢያው ይዘት ወይም ከዚህ ጣቢያ ጋር የተገናኙ የማንኛውም ጣቢያዎች ይዘት ትክክለኛነት፣ ሙሉነት፣ ወቅታዊነት፣ የሚጥሱ አለመሆናቸውን፣ መገበያየትን ወይም ብቃትን እንደሚረጋገጥ ዋስትና መስጠት አይችሉም እና አይሰጡም። የ SEIU ወገኖች ድረገፁ ከስህተት ነፃ ወይም ያለማቋረጥ የሚገኝ ወይም ድረገፁ ከቫይረሶች ወይም ሌሎች ጎጂ አካላት የፀዳ መሆኑንም ዋስትና አይሰጡም። የ SEIU ወገኖች በሶስተኛ ወገን የ SEIU ድረገፅ ወይም በማንኛውም ከፍ ያለ ግንኙነት ያለው ድረገፅ ወይም በማናቸውም ባነር ወይም ሌላ ማስታወቂያ ለቀረበ ምርት ወይም አገልግሎት አያረጋግጡም፣ ዋስትናም አይሰጡም ወይም ኃላፊነት አይወስዱም።
 6. የተጠያቂነት ገደብ በምንም አይነት ሁኔታ ከዚህ ድረገፅ ጋር በተገናኘ ለማንኛውም በተዘዋዋሪ፣ በአጋጣሚ፣ በልዩ፣ በቅጣት ወይም በምክንያት ለሚደርሱ ጉዳቶች I) የይዘት ስህተቶች፣ ችግሮች ወይም መዛባቶች፣ (II) የእኛን ድረገፅ ከመድረስ እና ከመጠቀም የሚከሰት የግል ጉዳት ወይም የንብረት ውድመት፣ ምንም አይነት ሁኔታ፣ (III) ያልተፈቀደ ደህንነቱ የተጠበቀ ሰርቨሮቻችንን ማግኘት ወይም መጠቀም እና/ወይም በውስጡ የተከማቸ ማንኛውም የግል መረጃ እና/ወይም የፋይናንስ መረጃ፣ (IV) ወደ ድረገፃችን ወይም ከድረገፃችን የሚተላለፉ መስተጓጎል ወይም መቋረጥ፣ (V) በማናቸውም የሶስተኛ ወገን ወደ ድረገጻችን ሊተላለፉ የሚችሉትን ሳንካዎች፣ ቫይረሶች፣ ትሮጃን ፈረሶች ወይም የመሳሰሉት እና/ወይም (VI) ስህተቶች ወይም ግድፈቶች በማናቸውም ይዘት ውስጥ ወይም በማንኛውም አይነት ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት የተለጠፈ፣ ኢሜይል የተላከ፣ የተላለፈ ወይም በሌላ መልኩ በ SEIU ድረገፅ በኩል በዋስትና፣ ውል፣ ከህግ ውጪ ወይም በማንኛውም ሌላ የህግ ንድፈ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ እና SEIU እንደነዚህ መሰል ጉዳቶች ሊደርሱ እንደሚችሉ ቢመከርም ባይመከርም እንዲገኝ የተደረገ ይዘትን ጨምሮ የ SEIU ወገኖች በምንም መልኩ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም። የ SEIU ወገኖች ለተጠቃሚ ይዘት ወይም ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን ስም ማጥፋት፣ ደስ የማያሰኝ ወይም ህገ-ወጥ ምግባር ተጠያቂ እንደማይሆኑ እና ከዚህ በላይ የተመለከተው የመጉዳት ወይም ጉዳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በእርስዎ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እውቅና ሰጥተዋል። የተወሰኑ የስቴት ህጎች በተዘዋዋሪ ዋስትናዎች ላይ ገደቦችን ወይም የተወሰኑ ጉዳቶችን ማግለል ወይም መገደብን አይፈቅዱም። እነዚህ ህጎች እርስዎን በሚመለከቱበት መጠን ልክ፣ በዚህ ስምምነት ውስጥ የተመለከቱት አንዳንድ ድንጋጌዎች ላይተገበሩ ይችላሉ። ከ SEIU ድረገፅ አጠቃቀምዎ እና በመድረስዎ ወይም የዚህን የተጠቃሚ ስምምነት በመጣስዎ ሳቢያ የሚነሱትን ማናቸውም እና ሁሉም የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ የ SEIU ወገኖችን ለመካስ እና ምንም ጉዳት የሌላቸውን ለመያዝ ተስማምተዋል። ይህ የማካካሻ ግዴታ ከዚህ የተጠቃሚ ስምምነት እና የ SEIU ድረገፅ አጠቃቀምዎ ይመለከታል።
 7. የተጠቃሚ ስምምነትን የመቀበል ችሎታ ከ18 ዓመት በላይ ወይም ነፃ የሆነ ልጅ መሆንዎን ወይም ህጋዊ የወላጅ ወይም የአሳዳጊ ስምምነት ያለዎት እና ውሎችን፣ ሁኔታዎችን፣ ግዴታዎችን፣ ማረጋገጫዎችን፣ ውክልናዎችን ለመግባት ሙሉ በሙሉ እንደሚችሉ እና ብቁ እና በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ውስጥ የተቀመጡ ዋስትናዎች እና ይህንን የተጠቃሚ ስምምነት እንደሚከብሩ እና እንደሚጠቡቁ ያረጋግጣሉ። በማንኛውም ጉዳይ፣ የ SEIU ድረገፅ ከ 13 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የታሰበ ስላልሆነ ከ 13 አመት በላይ መሆንዎን አረጋግጠዋል።
 8. ልዩ ልዩ ይህ የተጠቃሚ ስምምነት የህግ ግጭት መርሆዎችን ሳያካትት በዋሽንግተን ዲ.ሲ ውስጣዊ ተጨባጭ ህጎች መተዳደር መቻል አለበት። በእርስዎ እና SEIU መካከል በሙሉ ወይም በከፊል ከድረገፁ የሚነሱት ማናቸውም የይገባኛል ጥያቄዎች ወይም አለመግባባቶች በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው የፍርድ ቤት ችሎት ብቻ ይወሰንበታል። ይህ የተጠቃሚ ስምምነት ከግላዊነት ፖሊሲ እና SEIU የታተሙ ሌሎች ህጋዊ ማስታወቂያዎች በድረገፁ ላይ በተጠቃሚው ስምምነት ውስጥ ከተሰራው ማንኛውም ጉዳይ ጋር በተገናኘ በእርስዎ እና SEIU መካከል ያለውን አጠቃላይ ስምምነት የሚፈጥር ሲሆን ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን ይተካል። የዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ማንኛውም አቅርቦት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ትክክል እንዳልሆነ ከታሰበ የዚህ አይነት አቅርቦት ዋጋ-አልባነት የተቀሩት የዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ድንጋጌዎች ትክክለኛነት ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም፣ ይህም ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ሆኖ ይቆያል። የዚህ የተጠቃሚ ስምምነት የትኛውም ውል መተው እንደ ተጨማሪ ወይም ቀጣይነት ያለው ውል ወይም ሌላ ውል አይቆጠርም እናም SEIU በዚህ የተጠቃሚ ስምምነት ውስጥ ማንኛውንም መብት ወይም አቅርቦት አለመስጠቱ የዚህ አይነት መብት ወይም አቅርቦትን መተው ተደርጎ አይወሰድም። ይህ የተጠቃሚ ስምምነትና ማንኛውም በዚህ ስር የተሰጡ መብቶችና ፈቃዶች በእርስዎ ሊተላለፉ ወይም ሊመደቡ ባይችሉም በ SEIU ያለ ገደብ ሊመደቡ ይችላሉ። ይህ የተጠቃሚ ስምምነት እና በዚህ ውስጥ የተፈጠሩ መብቶች እና ግዴታዎች በተዋዋይ ወገኖች እና በተተኪዎቻቸው እና በተሰጡት ጥቅሞች ላይ ብቻ የሚተገበሩ እና የሚሸፈኑ ሲሆን በዚህ ስምምነት ወይም አመኔታ ስር በማንኛውም ሌላ ግለሰብ ማንኛውም መብት፣ መፍትሄ ወይም የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ በዚህ ስምምነት ውስጥ፣ የተገለፀ ወይም ተዘዋዋሪ፣ የታሰበ ወይም ሊሰጥ የሚችል ምንም ነገር የለም። እርስዎ እና SEIU ከድረገፁ ላይ የሚነሳ ወይም የተዛመደ ማንኛውም የድርጊት መንስኤ ከተከሰተ በኋላ በአንድ (1) አመት ውስጥ መጀመር እንዳለበት ተስማምተዋል። ያለበለዚያ፣ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ለዘለቄታው ክልክል ነው።

ይህ የተጠቃሚ ስምምነት ከኦክቶበር 6፣ 2021 ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።

በጋራ ጠንካራ ነን።