ስለ SEIU6

9,000+ አባላት ጠንካራ

SEIU6 Property Services NW በዋሽንግተን ስቴት ውስጥ ከ 9,000 በላይ የፅዳት ሰራተኞችን፣ የደህንነት መኮንኖች፣ የኤርፖርት ሰራተኞችን፣ የስታዲየም ሰራተኞችን እና አጋር የኢንዱስትሪ ሰራተኞችን ያቀፈ የሰው ሃይልን በኩራት ይወክላል። SEIU6 የስታዲየም ሰራተኞችንም እንዲሁም ፀጉር አስተካካዮችንም ይወክላል። በጋራ በመሆን አባላቶቻችን የሚገባቸውን ደመወዝ፣ ጥቅማ-ጥቅሞች እና እድሎች የማግኘት የተሻለ እድል አላቸው።

በርካታ የ SEIU6 አባላት እንደ ስፓኒሽ፣ ሶማሊኛ፣ ቬትናምኛ፣ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎችን የሚናገሩ ስደተኞች ናቸው። ሁሉም አባላት የፈለጉትን መረጃ እንዲያገኙና መብታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

SEIU6 የተመሰረተው በሲያትል የቲያትር ፅዳት ሰራተኞች ቡድን ሲሆን በ 1921 ከአገልግሎት ሰራተኞች አለም አቀፍ ህብረት ውስጥ አንዱ ሆነ። SEIU በሰሜን አሜሪካ ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የአገልግሎት ሰራተኞችን የሚወክል ሲሆን በሰራተኛ ንቅናቄ ውስጥ በጣም የተለያየ አባልነት እና አመራርነት በማግኘቱ ኩራት ይሰማዋል።

ተልዕኳችን

SEIU6 ሰራተኞች በስራ ቦታ ፍትህ እንዲጠይቁና የጎለበተ፣ ፍትሃዊ እና አስተማማኝ የወደፊት ተስፋን ለሁላችንም እንድንገነባ አቅም ይሰጣል። እኛ የመድብለ ባህላዊ፣ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪ፣ በጋራ ተግባር ለዘር እና ማህበራዊ ፍትህ የምንጥር ድርጅት ነን።

ተልዕኳችንን የምናሳካው በ፡-

የህብረታችን ድምፅ እና መሪዎች እንዲሆኑ አባላትን ማበረታታት፣ ማሰልጠን እና መደገፍ

በህብረታችን ቆይታ ውስጥ በንቃት የሚሳተፍ የተዋሃደና በመረጃ የተደገፈ አባልነትን ማዳበር

የህብረት አባልነት ጥቅሞችን ላልተደራጁ አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ለማዳረስና ኢንዱስትሪዎቻችንን እና የስራ ገበያዎቻችንን ለመቆጣጠር በትልቅ ጥረት የተገኘውን የአባሎቻችንን ትርፍ እና ደህንነት ለመጠበቅ መደራጀት

ደመወዝ እና የስራ ሁኔታን በማሻሻል እና ስራ ቦታ ውሳኔ ላይ የአባላትን ሚና በማስፋት ጠንካራ ህብረትን የሚገነቡ ኮንትራቶችን መደራደር

በሁሉም የመንግስት እርከኖች ውስጥ የሰራተኞች ድምፅ እንዲሰማ የፖለቲካ ሃይል መፍጠር

ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን መፍጠርና ማህበራዊ ፍትህን ማጎልበት

ትብብርን መፍጠር እና የዘር፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ ስጋታችንን ከሚጋሩ ሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት

በጋራ ጠንካራ ነን።