በሥነምግባር ሊከሰት የሚችልን ሁኔታ ለመመርመር ከእርስዎ ተቆጣጣሪ ወይም ስራ አስኪያጅ ጋር ወደ ስብሰባ ከተጠሩ የተለየ የውክልና መብት አለዎት። እነዚህ መብቶች “የዊንጋርተን መብቶች” የሚባሉ ሲሆን ከዚህ በታች ተጠቃለዋል።
- የሠራተኛ ማኅበር ሰራተኞች ተወካይ (Union Shop Steward) የመገኘት መብት አለዎት
- በዚያ የሰራተኞች ተወካይ ከፈለጉ፣ እሱን ወይም እሷን መጠየቅ አለብዎት
- ተቆጣጣሪዎ ወይም ስራ አስኪያጅዎ ከእርስዎ ጋር መገናኘት ለምን እንደፈለገ ካላወቁ፣ የሥነምግባር ጉድለት እርምጃ ሊያስከትል የሚችል ስብሰባ እንደሆነ ይጠይቁ
- አስተዳዳሪዎ የሰራተኞች ተወካይ እንዲያመጡ ካልፈቀደ፣ ጥያቄዎን በምስክር ፊት ይድገሙት። በስብሰባው ላይ ለመገኘት አሻፈረኝ አይበሉ፣ ነገር ግን ማንናቸውም ጥያቄዎች አይመልሱ። ማስታወሻ ይያዙ። ስብሰባው ካለቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ወደ የሰራተኞች ተወካዮ ይደውሉ።
- ከስብሰባው በፊት፣ በስብሰባው ወቅት እና ከስብሰባው በኋላ ከሰራተኞች ተወካዮ ጋር በግል የመነጋገር መብት አለዎት
- የሰራተኞች ተወካዮ በስብሰባው ላይ ንቁ ሚና የመጫወት መብት አለው። እሱ ወይም እሷ ምስክር ብቻ አይደለም/ችም።
“የዊንጋርተን መብቶች” በ 1975 ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ፣ NLRB v. J. Weingarten ላይ የተመሰረተ ነው።
ይህ መግለጫ ስራዎን ሊቆጥብልዎት ይችላል፡-
“ይህ ውይይት በምንም መንገድ ወደ ተግሳፅ ወይም መቋረጥ የሚመራ ከሆነ፣ የሰራተኞች ተወካይ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ያለ ውክልና፣ ለማንናቸውም ጥያቄዎች ወይም መግለጫዎች ምላሽ ከመስጠት እመርጣለሁ።
የሠራተኛ ማኅበር ውክልና
ከቃለ መጠይቁ በፊትም ሆነ በሚደረግበት ወቅት የሠራተኛ ማኅበር ውክልና መጠየቅ አለብዎት። አስተዳደሩ ይህንን መብት ለእርስዎ ማሳወቅ አይጠበቅቦትም።
ያለ ሠራተኛ ማኅበር ውክልና ለመቀጠል አሻፈረኝ ማለት
ቃለ-መጠይቅ አድራጊው ስለ ውክልና ፍላጎትዎ ሊነገረው ይገባል። በእርስዎ በኩል ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆን እንደ አለመታዘዝ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። አስተዳደሩ የእርስዎን ውክልና ካልፈቀደ በክፍሉ ውስጥ ይቆዩ፣ ግን ዝም ብለው ይቆዩ።
የጥፋተኝነት ወይም ከጥፋት ነፃ መሆንን የፅሁፍ ወይም ቃል መግለጫ አይስጡ
መግለጫ እንዲሰጡ ሊገደዱ አይችሉም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በጣም ትክክለኛው ምላሽ ምንም መግለጫ አለመስጠት ነው – ጥፋት የለብኝም ማለት እንደ መግለጫ ይቆጠራል።
ውክልና የማግኘት መብትዎን አሳልፈው አይስጡ
ያለ ውክልና ወደ ቃለመጠየቅዎ ከቀጠሉ የውክልና መብትዎን ትተዋል እናም ማንኛውንም መግለጫ በእርስዎ ላይ መጠቀም ይቻላል።
“የዊንጋርተን መብቶች” መደበኛ የስራ ግዴታዎችን ወይም የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ በአባላት እና ተቆጣጣሪዎች መካከል ለሚደረጉ የዕለት ተዕለት ንግግሮች አይተገበርም።