ይሳተፉ

ድምፅዎ ዋጋ አለው

ንቁ አባላት SEIU6 ን ጠንካራ ያደርጉታል። ለህብረታችን አዲስም ሆኑ የረዥም ጊዜ አባል፣ ድምፅዎ ጠንካራ ውሎችን ለማሸነፍ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና የተከበሩ የስራ ቦታዎችን በመጠበቅ እና የሚሰሩ ቤተሰቦች ለሚያስፈልጋቸው የፖሊሲ ለውጦች በመታገል ላይ ተጽዕኖን ሊያሳድር ይችላል።

ከታች ስላሉት ማናቸውም እድሎች የበለጠ ለማወቅ ወደ አባል ግብዓት ማዕከል በ 206-448-7348 ይደውሉ ወይም ከታች ያለውን ቅፅ ይሙሉ።

የሰራተኞች ተወካይ ይሁኑ

በስራ ቦታዎ ላይ ያለውን የሃይል ሚዛን ይለውጡ። SEIU6 የሰራተኞች ተወካይዎች በውል አፈፃፀም ውስጥ ከፍተኛ ባለሙያዎች ይሆናሉ እናም የስራ ባልደረቦቻቸው ለመብታቸው እንዲቆሙ ያበረታታሉ። የሰራተኞች ተወካይዎች አዲስ አባላትን ወደ ህብረታችን የሚቀበሉ ሲሆን ከአስተዳደሩ ጋር በሚደረጉ ስብሰባዎች እንደ ህብረት ተወካይ ሆነው ያገለግላሉ።

በፖለቲካ ንቁ ይሁኑ

SEIU6 በስራ ላይ ላሉ እና ከዚያ ውጪ ለሆኑም ሰራተኞች ጥብቅና ይቆማል። ለዚያም ነው በአካባቢ፣ በስቴት እና በብሄራዊ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ሚና የምንጫወተው። የ SEIU6 አባላት የፖለቲካ ኮሚቴውን በመቀላቀል፣ ለሰራተኛ ሃይል ፈንድ በመለገስ አሊያም ደግሞ ለእጩ ወይም ለጉዳይ ምርጫ በመቀስቀስ በፖለቲካው ሂደት ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ።

ኮሚቴ ይቀላቀሉ

የአዲስ አባል ልምድ ኮሚቴ

አዲስ አባላትን ወደ ህብረታችን በእንኳን ደህና መጣችሁ ይቀበላሉ እናም በስራ ቦታ መብታቸውን ለማስከበር ከሚያስፈልጋቸው ግብዓቶች ጋር ያገናኗቸዋል።

የግንኙነቶች ኮሚቴ

የ SEIU6 ኮሙኒኬሽን ኮሚቴ አባል በመሆን በህዝባዊ ንግግር እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ክህሎቶችን ያዳብራሉ። ዘመቻዎችን ለማፋፋም እና ስራ የሚሰሩ ቤተሰቦች ጉዳዮችን ለማራመድ በአካል እና በኦንላይን ድምፅ ለማሰማት ያግዛሉ።

የ Womxn ኮሚቴ

ሁሉም ሴት- የሚለዩ አባላት ወደ የ SEIU6 Womxn ኮሚቴ በእንኳን ደህና መጡ የሚቀበሉ ሲሆን ይህም የሰራተኛ ሴቶችን እና የቤተሰቦቻችንን ጥቅም በማሳደግ የህብረታችንን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ይቀርፃል። የ Womxn ኮሚቴ አባላት ለጾታ እኩልነት በውል ቋንቋ እና በስራ ቦታ ባህል ላይ ትግል በማድረግ የወደፊት ፍትሃዊ ራዕይን በመገንባት ላይ ናቸው።

የፖለቲካ ኮሚቴ

SEIU6 ለየትኞቹ ፖሊሲዎች መታገል እንደሚገባ፣ የትኞቹን እጩዎች መደገፍ እንዳለብን ለመወሰን ያግዛሉ እና የተመረጡ ባለስልጣናትን ለሰራተኛ ቤተሰቦች ተጠያቂ ለማድረግ ያግዛሉ። የ SEIU6 የፖለቲካ ኮሚቴ በፖለቲካ ጉዳይ ላይ ለመወያየት፣ እጩዎችን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እና በመጪው ምርጫ ላይ ቃሉን ለባልደረባ አባላት ለማድረስ በየወሩ ይሰበሰባል።

በህብረት ስብሰባ ላይ ይገኙ

SEIU6 በዓመት አራት ጊዜ ጠቅላላ የአባልነት ስብሰባዎችን በሁለተኛው ቅዳሜ በጃንዋሪ፣ ኤፕሪል፣ ጁላይ እና ኦክቶበር በ12፡30pm ላይ ያካሂዳል። አሁን ባለው የጤና ምክሮች ላይ በመመስረት ስብሰባዎች በአካል በመገኘት ወይም በኦንላይ የሚከናወኑ ናቸው። በኢንዱስትሪ የሚደረጉ ስብሰባዎች በየወሩ ለፅዳት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ኦፊሰሮች እና ለኤርፖርት ሰራተኞች ይካሄዳሉ።

በማህበራዊ አውታረ መረቦች ላይ ይገናኙ

በህብረታችን ዘመቻዎች እና ዝግጅቶች ላይ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት SEIU6 ን በፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም ይከተሉ።

አዘጋጃችንን ያግኙ

ስለ ህብረታችን፣ ስለ ኮንትራትዎና ስለ ወቅታዊ ዘመቻዎች እና ክንውኖች የበለጠ ለማወቅ የአንድ-ለ-አንድ ስብሰባ ወይም የስራ ቦታ ጉብኝትን ከአዘጋጁ ጋር ያቅዱ።

ይሳተፉ

በጋራ ጠንካራ ነን።